በ18ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ባሕር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ።

0
280

ባሕርዳር: መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ተቀራራቢ ውጤት ላይ የሚገኙት ባሕር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጠባቂ ጨዋታ ያከናውናሉ። ባሕርዳር ከተማ ከነበረበት የውጤት ማጣት እያገገመ ይመስላል።በመጨረሻ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን ረቷል። በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል። ቡናዎቹ የመጨረሻ ጨዋታቸው ላይ ሽንፈት አስተናግደዋል።

ሁለቱ ቡድኖች ሳቢ እግር ኳስን የሚጫወቱ በመኾናቸው አዝናኝ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የመጀመሪያ ዙር የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ጥሩ የኳስ ፍሰት የታየበት እና አቻ የተጠናቀቀ ነበር።

የኢትዮጵያ ቡና በ29 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ ሞገዶቹ በሦስት ነጥብ አንሰው ስድስተኛ ላይ ተቀምጠዋል። ጨዋታው ቀን 10 ሰዓት ይጀምራል።
ሀምበርቾ ከአዳማ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here