ባሕርዳር: መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዩሮፓ ሊግ ዛሬ ስምንት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ጨዋታዎቹ ወደ ቀጣይ ዙር የሚያልፉ ቡድኖችን ይለያሉ። የእንግሊዞቹ ሊቨርፑል ከስፓርታ ፕራግ፣ ብራይተን ከሮማ እና ዌስትሃም ከፍራይቦርግ ይጫወታሉ።
በመጀመሪያው ጨዋታ ሊቨርፑል ስፓርታ ብራግን 5 ለ 1 መርታቱ ይታወሳል። ብራይተን በሮማ 4 ለ 0 የተሸነፈ ሲኾን፣ ዌስትሃም በፍራይቦርግ 1ለ 0 ተረቷል።
በሌሎች ጨዋታዎች ቪያሪያል ከማርሴ፣ አትላንታ ከስፓርቲንግ፣ ባየርሊቨርኩሰን ከቋራባግ ዛሬ ይጫወታሉ። ሬንጀርስ ከቤኔፊካ፣ ስላቪያ ፕራግ ከኤሲሚላን ሩብ ፍጻሜ ለመግባት የሚደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ናቸው።
በተያያዘ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች የተከናወኑ ሲኾን አትሌትኮ ማድሪድ እና ቦሩሲያ ዶርትመድ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።
አትሌቲኮ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኢንተር ሚላን 1 ለ 0 ተሸንፎ የነበር።የምሽቱ ጨዋታ ደግሞ 2 ለ 1 አሸንፏል። በደርሶ መልስ ውጤት ሁለቱ ክለቦች አቻ በመኾናቸው በመለያ ምት አትሌትኮ ማድሪድ አሸናፊ ኾኗል።
ቦሩሲያ ዶርትመድ ደግሞ ፒኤስቪን 2 ለ 0 አሸንፎታል። የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋት አንድ እኩል መጠናቀቁ ይታወሳል። ዶርትመንድ በደርሶ መልስ 3 ለ 1 በኾነ ውጤት ሩብ ፋጻሜ ገብቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!