አሠልጣኙ ከሥራቸው ለቀቁ፡፡

0
365

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ2023/2024 በጣልያን ሴሪኤ እየተሳተፉ ከሚገኙት 20 ቡድኖች መካከል በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ አቨርሳ የሚመራው ሌሴ አንዱ ነው።

እሑድ የሌሴ እና የሂላስ ቬሮና ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ ላይ የ48 ዓመቱ አሠልጣኝ ሮቤርቶ ዲ አቨርሳ ቡድናቸው በሂላስ ቬሮና 1ለ0 መሸነፉን ያረዳው የፊሽካ ድምጽ እንደተሰማ በንዴት ከመቀመጫቸው በመነሳት የተቃራኒን ቡድን አጥቂ ቶማስ ሄንሪን በጭንቅላታቸው ይነርቱታል።

ይህኔ ተመልካቹ ከፍተኛ ቁጣውን አሰምቷል። የዕለቱ ዳኛም “ጅብ ከሄደ.” ቢኾንም በቀይ ካርድ አሠልጣኙን ቀጥተውታል።ሰውየው ስለፈጸሙት አስነዋሪ ድርጊት ለስታዲዮ ቪያ ዴል ማሬ ሲናገሩ “የፈጸምኹት ጥሩ ያልኾነ ድርጊት ‘የማይታመን ‘ ነው” በማለት መጸጸታቸውን ገልጸዋል።

ይህንን ተከትሎም አሠልጣኝ ሮቤርቶ ዲ አቨርሳ ከሥራ ገበታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። የሌሴ ቡድን ካደረጋቸው 28 ጨዋታዎች በአምስቱ አሸንፎ፣ በ10 አቻ ተለያይቶ እና በ13 ጨዋታዎች ተሸንፎ በ25 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here