ተተኪዎችን ለማፍራት ታስቦ የተዘጋጀ የብስክሌት ውድድር በደሴ ከተማ ተካሄደ ።

0
219

ባሕርዳር: የካቲት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
ውድድሩ በከተማ አሥተዳደሩ በፕሮጀክት በታቀፉ በታዳጊዎች የተጀመረ ሲኾን በአዋቂዎች 50 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ውድድር ተካሂዷል።

የውድድሩ አለማ ስፖርቱን ለማነቃቃት እና ተተኪዎችን ለማፍራት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል። በአዋቂዎች ፍቅረማሪያም፣ ጀግናው ደጀን ፣ አወቀ የጎራው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። የተዘጋጀላቸውን የሜዳሊያ ፣ የገንዘብና የምስክር ወረቀት ከእለቱ የክብር እንግዳ እጅም ተቀብለዋል።

10 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የፕሮጀክት የታዳጊዎች ውድድር ደግሞ አብራር አብዱ አንደኛ ፣ ኢብራሂም ተሾመ ሁለተኛ እንዲኹም መድኅን ወንድፍሬ ሦስተኛ በመኾን የሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ኹነዋል ። ውድድሩ በቀጣም በየወሩ እንደሚቀጥል ከደሴ ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here