“ጥሩ መሸናነፍ እንደሚታይበት የሚጠበቀው” የባሕር ዳር ከተማ እና መቻል ጨዋታ

0
303

ባሕርዳር: የካቲት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ከተማ ከገጠመው የውጤት ቀውስ ለመውጣት ጥረት እያደረገ ነው።ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ሲረታ በሌላኛው አቻ መውጣቱ በተከታታይ ከገጠመው ሽንፈት አኳያ ጥሩ የሚባል ውጤት ነው።

ሞገዶቹ በሁለተኛው የውድድር ዓመት የተሻለ ጊዜን ለማሳለፍም ተጫዋቾችን አስፈርመዋል። የጣና ሞገዶቹ በደረጃ ሰንጠረዡ 6ተኛ ላይ ሲቀመጡ ከመሪው ንግድ ባንክም የ12 ነጥብ ልዩነት አላቸው።

መቻል ዘንድሮ ጥሩ የውድድር ዓመትን እያሳለፈ ነው።በደረጃ ሰንጠረዡ ንግድ ባንክን እየተከተለ ነው። በውድድሩ ሁለተኛ አጋማሽ የመጀመሪያ ጨዋታ ያስተናገደው ሽነፈት ከመሪነቱ እንዲወርድ አስገደደው እንጅ የሊጉ መሪም ነበር።

ሁለቱ ቡድኖች የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፍ ይበልጥ የዋንጫ ተፎካካሪ ለመኾን ጥሩ ፍክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። እንደ ኢትዮ ሶከር መረጃ በባሕር ዳርም ይኹን መቻል በኩል በጉዳትም ይኹን ቅጣት ጨዋታው የሚያልፈው ተጫዋች የለም። ነገር ግን የጣና ሞገዶቹ ቡድኑን ብዙም ካላገዘው አጥቂው ሱሌማን ትራኦሬ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።

ባሕር ዳር ከተማ እና መቻል ሰባት የእርስ በእርስ ግንኙነት ያላቸው ሲኾን ሦስቱን መቻል አሸንፏል። በሁለቱ ባሕር ዳሮች ድል ሲቀናቸው ሁለቱን አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው ምሽት 1:00 ይጀምራል።

ቀደም ብሎ በሚጀምር የዛሬ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከነማ ከሻሼመኔ ከተማ ጋር ይጫወታል። ሀዋሳዎች በሊጉ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ ሻሼመኔዎች ደግሞ 14ኛ ላይ ይገኛል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here