ባሕርዳር: የካቲት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኮፐን ሀገንን የገጠመው ማንቸስተር ሲቲ 3 ለ 1 አሸንፏል።በተመሳሳይ የመጀመሪያውን ጨዋታ 3 ለ 1 አሸንፎም ነበር። የእንግሊዙ ክለብ በደርሶ መልስ 6 ለ 2 በኾነ ውጤት የሩብ ፍጻሜ ቦታውን አረጋግጧል።
የስፔኑ ሪያል ማድሪድም ስምንቱ ውስጥ መግባቱን አረጋግጧል። ከአርቢ ሊፕዚንግ ጋር የተጫወተው ማድሪድ አንድ አቻ ጨዋታውን ጨርሷል።ነገር ግን በመጀመሪያው ዙር ባስመዘገበው የ2 ለ 1 ውጤት ተጠቃሚ ኾኗል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!