ባየርን ሙኒክ አሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶን ለመቅጠር ድርድር ላይ መኾኑ ተገለጸ።

0
289

ባሕር ዳር: የካቲት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ቡድን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ላይ ከአሠልጣኝ ቶማስ ቱቸልን ጋር እንደሚለያይ ይፋ አድርጓል።

ይህንን ተከትሎም በምትካቸው የባየር ሊቨርኩሰኑን አሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶን ወደ ቡድናቸው ለማምጣት ንግግር ጀምረው በመርኽ ደረጃ መስማማታቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

በአሁኑ ወቅት በዣቢ አሎንሶ እየሠለጠነ የሚገኘው ባየር ሌቨርኩሰን በቡንደስሊጋው እስካሁን 24 ጨዋታዎችን አድርጎ በ64 ነጥብ በመሪነት ወደ ዋንጫው እየገሰገሰ ይገኛል። ሻምፒዮንም ይኾናል ተብሎ ተገምቷል።

በአንጻሩ በቶማስ ቱቸልን የሚሠለጥነው ባየርን ሙኒክ በ24 ጨዋታዎች 54 ነጥብ በመያዝ እና ከመሪው በ10 ነጥብ ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል።

በጀርመን ቡደስሊጋ የ2023/2024 የውድድር ዘመን ኮሎኝ በ17 ነጥብ 16ኛ፣ ሜይንዝ በ16 ነጥብ 17ኛ እንዲኹም ዳርምስታድት 98 በ13 ነጥብ 18ኛ ደረጃን በመያዝ በወራጅ ቀጣናው ውስጥ እንደሚገኙ ዘገባው ጨምሮ አስታውሷል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here