ኬንያ የስፖርት ከተማ ልትገነባ ነው፡፡

0
368

ባሕር ዳር: የካቲት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኬንያ መንግሥት ታላንታን የተባለችውን ከተማ የስፖርት ከተማ ለማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ (ዶ.ር) ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ የታላንታ ስፖርት ከተማን የመሰረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ ባሰሙት ንግግር የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ እና የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት በዚች ከተማ እንዲኾን የሚያገለግል ነው ብለዋል።

ስታዲየሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኾኖ ስለሚገነባ የሀገሪቱን የስፖርት ቱሪዝም ያሳድጋል ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።ስታዲየሙ የአትሌቲክስ፣ የቴንስ፣ የራግቢ፣ የመረብ እና የቅርጫት ኳስ ጨዋታዎችን እንዲያስተናግድ ኾኖ ይገነባል ነው የተባለው።

ስታዲየሙ 46 ሄክታር የሚሸፍን ሲኾን በቻይና መንገድ እና ድልድይ ኮርፖሬሽን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይገነባል ነው የተባለው። የታላንታ ሰታዲየም 60ሺህ ዘመናዊ ወንበሮች ይኖሩታል ተብሏል።

የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንያ ከስታዲየሙ ግንባታ ጎን ለጎን የታላንታ ስፖርት ከተማን ለመገንባት 472 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የናይሮቢ-ሞምባሳ ስታንዳርድ ጌጅ የባቡር መስመር ይገነባል። የናይሮቢ ሞጃ የፍጥነት መንገድም አንዱ የግንባታው አካል ይኾናል።

ዘመናዊ መንደር፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ አየር መረፊያ፣ ሱፐር ማርኬት፣ የተሟላ የቴሌኮም እና የሀይድሮ እንዲኹም የሶላር ኀይል ስለሚኖረው “በታላንታ ከተማ 24 ሰዓት ፀሐይ አትጠልቅም” ሲሉ ኬንያን ሄራልድ እና ፒዩፕል ዴይሊ ዘግበዋል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here