አርሰናል የዋንጫ ተፎካካሪነቱን ለማጠናከር ከሸፊልድ ጋር ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል።

0
406

ባሕርዳር: የካቲት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የለንደኑ ክለብ አርሰናል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተሻለ የዋንጫ ተፎካካሪ ነው ያስባለውን አቋም እያሳየነው።ቡድኑ በ26 የሊጉ ጉዞ 58 ነጥብ በመሰብሰብ ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲን በቅርብ ርቀት እየተከተለ ነው።ዛሬ ሼፊልድን ማሸነፍ የሚችል ከኾነም ከሁለቱ ቡድኖች ይበልጥ በመቅረብ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን ያስቀጥላል።

ቡድኑ ባለፈው ዓመት ፕሪምየር ሊጉን ለረዥም ጊዜ መምራት ችሎ ነበር።ነገር ግን በሁለተኛው የውድድር ዘመን በተደጋጋሚ ነጥቦችን በመጣል ዋንጫውን በማንቸስተር ሲቲ ተነጥቋል።
በዚህ ዓመት የተሻለ ወጥ አቋም ያለው አርሰናል እየታየ ነው አንደ ቢቢሲ ዘገባ።በእስካሁን ጉዞው 18 ጨዋታዎችን አሸንፏል።አራት ጊዜ ነጥብ ተጋርቶ በአራቱ ሽንፈት አስተናግዳል።ይሄ አምና በተመሳሳይ የጨዋታ ቁጥር ከነበረው ጥንካሬ የተሻለ ነው።

በተጨማሪም ባለፈው ዓመት በሲቲ በደርሶ መልስ መሸነፉ ዋንጫውን ለማጣቱ በምክኒያትነት ተነስቶበት የነበረ ሲኾን ዘንድሮ ሲቲን በሜዳው ማሸነፍን ጨምሮ ትልልቅ የሚባሉ ቡድኖች ላይ ነጥብ መውሰዱ ጥንካሬው ነው።

በአንጻሩ ባለፈው ዓመት ለአርሰናል የዋንጫ ጉዞ እንቅፋት የነበረው ማንቸስተር ሲቲ ነበር።ዘንድሮ ግን ከሲቲ በተጨማሪ ሊቨርፑል በተለየ ጥንካሬ ሊጉን መምራቱ ለመድፈኞቹ የዋንጫ ጥም ሌላ እንቅፋት ነው ተብሏል።

የሊቨርፑል እና ሲቲ ጥንካሬ እንዳለ ኾኖ የአርቴታው ቡድን በዋንጫው ፍክክር ለመዝለቅ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይጠበቅበታል።በ27ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ከሜዳው ውጭ ሼፊልድ ዩናይትድን የሚገጥምበት ጨዋታም ይጠበቃል።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here