ሌብሮን ጀምስ ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ አዲስ ክብረ ወሰን ያዘ።

0
239

ባሕርዳር: የካቲት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሌብሮን ሬይሞን ጄምስ አሜሪካዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ነው። ጀምስ ቅርጫት ኳስን ለ21ዓመታት ሲጫወት ባሳየው እጹብ ድንቅ ብቃት “ኪንግ ጀምስ” የሚል ቅጽል ስም ተችሮታል።

ሌብሮን እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2018 ጀምሮ ለሎስ አንጀለስ ሌከርስ ቡድን በመሰለፍ ላይ ነው። ከሰሞኑ ሎስ አንጀለስ ሌከርስ ከዴንቨር ኑግትስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ጀምስ 26 ቅርጫት አስቆጥሮ ቡድኑ 124 ለ114 አሸንፏል።

ሌብሮን ጀምስ ከ2003 ጀምሮ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ያስቆጠራቸው ቅርጫቶች ወደ ነጥብ ሲቀየር 40ሺህ በማድረስ በአብዱል-ጀባርን በ38 ሺህ 3 መቶ 87 ነጥብ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ተረክቧል።

ጀምስ በአሜሪካ የወንዶች ብሔራዊ የቅርጫት ኳስ ቡድን በመመረጥም ሁለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፏል። እንደ አውሮፖ አቆጣጠር በ2004 በተካሄደው የአቴንስ ኦሎምፒክ አሜሪካ የብር ሜዳሊያ እንድታገኝ ዋናውን ሚና ተጫውቷል ሊብሮን ጀምስ።

በ2008 በቤጂንግ እና በ2012 በለንደን ኦሎምፒኮች ከቡድን አጋሮቹ ጋር ሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ እንድትሸለም ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ማበርከቱም ይታወቃል።
የሎስ አንጀለስ ሌከርስ ቡድን አሠልጣኝ ዳርቪን ሃም “በጀምስ ስኬት ደስተኛ ነኝ፤ ለክብሩም ባርኔጣዬ አንስቼ ገልጨለታለኹ” ብለዋል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here