ዋይኒ ሩኒ ኤቨርተን እና ማንቸስተር ዩናይትድን የማሠልጠን ሕልም እንዳለው ተናገረ።

0
254

ባሕር ዳር: የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዋይኒ ሩኒ በእንግሊዝ በፕሪሜየር ሊግ ኤቨርተን እና ማንቸስተር ዩናይትድን የማሠልጠን ሕልም እንዳለው ተናግሯል።

ሩኒ 16 ዓመታትን በጉዲሰን ፓርክ እና ኦልድትራፎርድ በተጫዋችነት ቆይታው አይረሴ ዘመንን አሳልፏል። ስለኾነም በእነዚህ ቡድኖች ውስጥ መሥራት እንደሚፈልግ ቢቢሲ ስፖርት በድረ ገጹ አስነብቧል።

አሠልጣኝ ዋይኒ ምንም እንኳን በአሜሪካ የዲሲ ዩናይትድ ቡድንን እያሠለጠነ ካደረጋቸው 53 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለ በ14 ጨዋታዎች ብቻ ነበር። በመኾኑም ቡድኑ ባጋጠመው የነጥብ ማሽቆልቆል ምክንያት ለመልቀቅ ተገድዷል።

ሩኒ ከዲሲ ዩናይትድ አሠልጣኝነቱ ከወረደ በኋላ በሻምፒዮን ሽፑ የሚሳተፈውን የበርሚንግሃም ቡድንን ለማሠልጠን ተስማምቷል። በቆይታውም ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች መርታት የቻለው በሁለቱ ብቻ ነው። በዘጠኝ ጨዋታዎች ተሸንፏል

ሰውየው በበርሚንግሃም ሲሾም የክለቡ ደረጃ ስድስተኛ የነበረ ሲኾን ቀስበቀስ ወደ ወራጅ ቀጣናው እየተጠጋ ሄደ። ስለኾነም ከቡድኑ ለመሰናበት ተገድዷል። ሩኒ ለዴይሊ ሜይል “ማንቸስተር ዩናይትድን ወይም ኤቨርተን የማሥተዳደር አላማ አለኝ። በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥም ወደ አንዱ ቡድን ለመግባት የሚያስችል ሁኔታ ላይ እንዳለኹ ለማረጋገጥ ራሴን ወደ አሥተዳደር መመለስ እፈልጋለሁ” ብሏል።

ዋይኒ ሩኒ ለማንቸስተር ዩናይትድ እና ለልጅነት ክለቡ ኤቨርተን 208 ግቦችን በማስቆጠር በፕሪሜየር ሊጉ ታሪክ የሦስተኛ ደረጃን መቆናጠጡን ቢቢሲ አስታውሷል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here