በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን በግብጹ ዛማሌክ እና ጊኒው ሶአር መካከል የሚደረገው ጨዋታ በኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመራል።

0
261

ባሕር ዳር: የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ዳኞች በሳምንቱ መጨረሻ ዛማሌክ እና ሶአር የሚያደርጉትን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታ ይመራሉ ነው የተባለው።

የ2023/24 የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ የፊታችን እሑድ በካይሮ ስታዲየም ይካሄዳል። ምድብ ሁለት ላይ የሚገኙት የግብጹ ዛማሌክ ከጊኒው ሶአር ክለብ ጋር ምሽት 2 ሰዓት ይጫወታሉ።

ጨዋታውንም ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንዲመሩት በካፍ ስለመመረጣቸው ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። በዋና ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ፣ ረዳቶቹ ፋሲካ የኋላሸት እና ሙስጠፋ መኪ ኾነው ተመርጠዋል። አራተኛ ዳኛ ኾነው የሚያገለግሉት ደግሞ ዶክተር ኃይለየሱስ ባዘዘው ናቸው።

በመጀመሪያው የምድቡ ጨዋታ ዛማሌክ ከሜዳው ውጪ 4 ለ 0 ረትቷል፤ ምድቡንም ዛማሌክ በበላይነት እየመራ ይገኛል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here