በ6ኛው የአፍሪካ የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና የተሳተፈው የልዑካን ቡድን ወደ ሀገር ተመልሷል።

0
256

ባሕርዳር: የካቲት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የልዑካን ቡድኑ ከሌሊቱ 7 ሰዓት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የልዑካን ቡድኑን የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የአበባ ጉንጉን በጋራ አበርክተዋል ።

የአትሌቲክስ ቡድኑ 12 ሀገራት በተሳተፉበት 6ተኛው የአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኬንያን በመከተል ሁለተኛ ኾኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here