ባሕር ዳር: የካቲት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በሞሮኮ ለሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 52 ሀገራት በማጣሪያ ጨዋታዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጨዋታው የቅድመ ማጣሪያ እና የማጣሪያ ጨዋታዎች እንደሚደረጉ ልብ ይሏል።
የቅድመ ማጣሪያ ድልድሉም ከሰሞኑ በግብጽ መዲና ካይሮ ይፋ ተደርጓል። የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት በፊፋ የደረጃ ልየታ ዝቅተኛ ደረጃ የተሰጣቸው ስምንት ሀገራት ናቸው።
ጨዋታውንም በሜዳቸው እና ከሜዳቸው ውጪ በማድረግ በጥሎ ማለፉ አሸናፊ የሚኾኑት አራት ሀገራት ብቻ ዋናውን የማጣሪያ ውድድር ይቀላቀላሉ ሲል ካፍ ኦንላይን ኒውስ ዘግቧል።
የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከመጋቢት 20 እስከ 26/2024 እንደሚካሄዱም ዘገባው አትቷል። በዚህም መሰረት ሶማሊያ ከኢስዋቲኒ፣ ሳኦቶሜ ከደቡብ ሱዳን፣ ቻድ ከሞሪሸስ እንዲሁም ጅቡቲ ከላይቤሪያ የሚጫወቱ ይኾናል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!