ባሕር ዳር: የካቲት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ካፍ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር እስከ የካቲት ለማካሄድ አቅዶ እንደነበር ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞቴፔ አስታውሰዋል። ይሁንና የዓለም እግር ኳስ ማኀበር (ፊፋ) የዓለም የክለቦች ዋንጫን ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 13 በዩናይትድ ስቴትስ ለማካሄድ የውድድር መርሐ ግብር በመቁረጡ ሁለቱ ትልልቅ ጨዋታዎች እንዳይደራረቡ ለማድረግ ነው ተብሏል።
ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የጨዋታዎች ድልድል ከሰሞኑ በካይሮ ይፋ እንደሚደረግ ካፍ አስታውቋል።
በድልድሉ መሠረት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ብሔራዊ ቡድኖች በፊፋ ዝቅተኛ ደረጃ የተሰጣቸው ይኾናሉ። እነሱም፦ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሳኦቶሜ፣ ቻድ፣ ሞሪሸስ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ላይቤሪያ እና ስዋዚላንድ ናቸው።
በጨዋታው አሸናፊ የሚኾኑት አራቱ ከ44 ሀገራት ጋር የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ነው የተባለው።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!