ባሕርዳር: የካቲት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ባለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተካሄዱ ነው።ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች እንዲካሄዱ ቀጠሮ ሲያዝላቸው ኢንተር ሚላን ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚገናኙበት ጨዋታ የተሻለ መሸናነፍ እንደሚታይበት ተጠብቋል።
የአምናው የውድድሩ የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተር ሚላን ዘንድሮም ጠንካራ ቡድን ነው። በጣሊያን ሴሪ ኤ ድንቅ ብቃቱንም እያሳየ ነው። በሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ጨዋታዎች ምድብ አራትን በበላይነት ካጠናቀቀው ሪያል ሶሴዳድ ጋር እኩል 12 ነጥብ ሠብሥቦ በግብ ክፍያ ተበልጦ ነው ሁለተኛ ኾኖ ያጠናቀቀው።
አትሌቲኮ ማድሪድ በላሊጋው ወጥ አቋም ላይ ባይገኝም በሻምፒዮንስ ሊጉ ላይ ግን ቡድኑ ጠንካራ ነው።ምድብ አምስትን በበላይነት ያጠናቀቀውም 14 ነጥቦችን ሠብሥቦ ነው።
ሌላኛው የዛሬ ጨዋታ የሆላንዱ ፒስቪ ከጀርመኑ ቦርሲያ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት ነው።ፒስቪ አርሰናልን በመከተል ከምድብ ሁለት አሁን የተገኘበት ቦታ ደርሷል።
ቦርሲያ ዶርትሙንድ በበኩሉ የሞት ምድብ በተባለው ፒስጂ፣ ኤሲሚላን እና ኒውካስትል በነበሩበት ምድብ የምድቡ አሸናፊ መኾኑ ይታወሳል።
በአስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!