ባሕርዳር: የካቲት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሪሜየር ሊጉ የውድድሩን አጋማሽ በማጠናቀቁ የእረፍት ጊዜ ላይ ይገኛል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ የበቁ ቡድኖች ጨዋታ ያደርጋሉ።
ዛሬ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ይጫወታሉ። ነገ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ድቻ የሚገናኙ ሲኾን፣ ትልቅ ትኩረት ያገኘው የፋሲል እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ሐሙስ ይካሄዳል። አርባ ምንጭ ከሀዋሳ አርብ የሚደረግ ጨዋታ ነው።
ጨዋታዎቹ በአዲስ አበባው አበበ ቢቂላ ሜዳ ቀን 9 ሰዓት ይከናወናሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!