ባሕር ዳር: የካቲት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ31 ዓመቱ ግብጻዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞሐመድ ሳላህ በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ልቆ ይወጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡
ይሁን እና ሳላህ በደረሰበት ጉዳት ጨዋታውን አቋርጦ ለሕክምና ወደ ሊቨርፑል ማቅናቱ ይታወሳል፡፡
ይህ የ31 ዓመቱ ተጫዋች በደረሰበት ጉዳት ከግብጽ ብሔራዊ ቡድኑ ጋር እንደታሰበው መሰለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡
የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተሸንፋ በጊዜ ከጨዋታው ውጪ ኾናለች፡፡
የግብጽ የስፖርት ቤተሰብን ከብሔራዊ ቡድኑ ሽንፈት በመለስ ያስጨነቀው የሳላህ ጤንነት ነበር፡፡ ከሰሞኑ ተጫዋቹ ከጉዳቱ አገግሞ ሥልጠና መጀመሩን ካፍኦንላይን ዘግቧል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!