ባሕርዳር: የካቲት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሻምፒዮንስ ሊጉ በዛሬ መረሐ ግብሩ ፒስጅን ከሪያል ሶሴዳድና ባየርሙኒክን ከላዚዮ ያገናኛል።ጨዋታዎቹ የተሻለ ፍክክር እንደሚታይባቸውም ይጠበቃል።
ትናንት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ማንቸስተር ሲቲና ሪያልማድሪድ አሸንፈዋል።ከሜዳው ውጭ ኮፐንሀገንን የገጠመው ማንቸስተር ሲቲ 3 ለ 1 በማሸነፍ የቀጣይ ሥራውን አቅሏል።
በወሳኝ ተጫዋቾች ጉዳት ስጋት ላይ የነበረው ሪያል ማድሪድም ጀርመን ላይ አርቢ ሊፕዚንግን ድል አድርጓል።ጨዋታው አንድ ለባዶ የተጠናቀቀ ሲኾን የመልሱን ጨዋታ በሜዳው ለሚያደርገው ማድሪድ ጥሩ ውጤት ኾኗል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!