ባሕር ዳር: የካቲት 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቤልግሬድ የቤት ውስጥ የ800 ሜትር ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ የቦታውን ፈጣን ሰዓት እና ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች።
በቤልግሬድ የቤት ውስጥ የ800 ሜትር ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ በ 1:59:66 ሰዓት የቦታውን ፈጣን ሰዓት እና ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች፡፡ እንዲሁም በውድድሩ አትሌት ትግስት ግርማ 2:00.21 በኾነ ሰዓት በመግባት 2ተኛ ኸና ማሸነፏን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!