በሜክሲኮ ተጀምሮ በአሜሪካ የሚፈጸመው የዓለም ዋንጫ!

0
283

ባሕር ዳር: ጥር 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሀገራት ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ናቸው፡፡ በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ሦስት ሀገራት ሲያዘጋጁ ይህ የመጀመሪያው ይኾናል፡፡
ጨዋታው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሰኔ 11/2026 ተጀምሮ ሐምሌ 19/2026 እንዲጠናቀቅ መርሐ ግብር ወጥቶለታል፡፡የስፖርት ልዑካን ቡድኖች የሚያርፉባቸው በአሜሪካ 11፣ በካናዳ ሁለት፣ እና በሜክሲኮ ሦስት ከተሞች ተለይተዋል፡፡ በሦስትዮሽ በሚዘጋጀው የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የ48 ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች 104 ጨዋታዎችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እንዳሉት የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ 87 ሺህ 523 ተመልካች በሚያስተናግደው በሜክሲኮ ሲቲው የኢስታዲዮ አዝቴካ ስታዲየም ይደረጋል ብለዋል።

ኢንፋንቲኖ አክለውም የፍፃሜው ጨዋታ ኒውዮርክ ኒው ጀርሲ በሚገኘው እና 82 ሺህ 500 ተመልካች በሚይዘው “ሜት ላይፍ” ስታዲየም ይደረጋል ማለታቸውን ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here