ባሕር ዳር: ኅዳር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን (ቀይ ቀበሮዎቹ) ኬንያን 3 ለ 0 በኾነ ውጤት በማሸነፍ ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፋቸው እንኳን ደስ አለን ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በግል የማኅበራዊ ገጻቸው።
በስፖርቱ ዘርፍ ታዳጊዎች ላይ በርትተን ከሠራን እግር ኳሳችን በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፋዊ መድረኮች ከፍ የሚልበት ጊዜ ሩቅ እንደማይኾን ይህ ስኬት አመላካች ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የዛሬው ውጤት እንዲገኝ ሚናችሁን ለተወጣችሁ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን በማቅረብ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን



