ቡድኑ ድሉን ያረጋገጠው ዛሬ ከኬንያ አቻው ጋር በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታድየም ባደረገው ጨዋታ 3ለ0 በማሸነፉ ነው፡፡
የማሸነፊያ ግቦቹን የውድድሩ ክስተት ዳዊት ካሳው እና አምበሉ ቢንያም፣ብሩክ አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተመልሷል፡፡
የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች የዋንጫ ውድድሩ በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡
ዛሬ ከቀኑ 9፡ 30 ላይ ዩጋንዳ እና ታንዛኒ የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በዋሴ ባየ



