ብላክ ላዮን የሰርከስ ቡድን በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ።

0
246

ባሕር ዳር: ጥር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያን ወክሎ ወደ ጣሊያን በማቅናት በዓለም አቀፍ የሰርከስ ጥበብ ላይ የተሳተፈው ብላክ ላዮን የሰርከስ ቡድን የዓለምን ሪከርድ ሰብሮ አድናቆትን አትርፏል። የሰርከስ ቡድኑ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ መስፈሩም ተገልጿል፡፡

የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ በሰርከስ ኪነ ጥበብ የዓለምን ሪከርድ በመስበር የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም መድረክ ከፍ ላደረጉት የቡድኑ አባላት አቀባበል አድርገዋል፡፡ ለቡድኑ እውቅና በመስጠት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክትም አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰርከስ ማኅበራት ጥምረት ፕሬዚዳንት ተክሉ አሻግር የብላክ ላዮን የሰርከስ ቡድን ውጤት የመጀመሪያ እንዳልሆነና ከዚህ በፊት በኢትዮጵያውያን ዘጠኝ የዓለምን ክብረ ወሰን መሰበሩን ገልጸዋል፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here