ባሕር ዳር: ኅዳር 12/2018 ዓ.ም (አሚኾ) ነገ ቀን 9:00 በደረጃ ሰንጠረዡ 17ኛ ላይ የሚገኘው በርንሌይ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ቼልሲን ይጋብዛል።
ምሽት 12:30 ላይ በርንማውዝ ከዌስትሃም፣ ብራይተን ከብሬንትፎርድ፣ ፉልሃም ከሰንደርላንድ፣ ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎሬስት፣ ዎልቭርሃምፕተን ወንደረርስ ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ምሽት 2:30 ደግሞ ኒውካስትል ከማንቸስተር ሲቲ ይጫወታሉ።
ሊጉ እሑድም ቀጥሎ ሲውል ሊድስ ዩናይትድ ከአስቶንቪላ ቀን 11:00 ላይ የሚጫወቱ ይኾናል። ምሽት 1:30 አርሰናል ከቶትንሃም ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ቢቢሲ በድረ ገጹ አስነብቧል።
ሊጉን አርሰናል በ26 ነጥብ በመምራት ላይ ይገኛል። ማንቸስተር ሲቲ በ22 ነጥብ በሁለተኛነት ይከተላል። ቼልሲ በ20 ነጥብ በሦስተኛነት ተቀምጧል።
ዌስት ሃም፣ ኖቲንግሃም ፎሬስት እና ዎልቭርሃምፕተን ወራጅ ቀጣና ላይ ይገኛሉ።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



