በጎንደር ከተማ በ26 ሕዝባዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ላይ ሰፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው።

0
15
ጎንደር: ኅዳር 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን በኅብረት ሢሠሩ አሚኮ ያገኛቸው ተሳታፊዎች ጤናቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጋራ እየሠሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።
በኅብረት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከሚያደርጉት ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሰይድ ኡስማን በተከታታይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረጋቸው ከ110 ኪሎ ግራም ወደ 95 ኪሎ ግራም ክብደታቸውን መቀነስ እንደቻሉ ተናግረዋል።
ሌላኛዋ ተሳታፊ ወይዘሮ ፋሲካ ብርሌው ስፖርት መሥራት ከጀመሩ ከአምስት ዓመት በላይ እንደኾናቸው ገልጸዋል። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ጤናማ መኾን እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ክብደት መቀነስ እና ከባድ የራስ ሕመማቸውን ማስታገስ እንዳስቻላቸው ለአሚኮ የተናገሩት አቶ ንጉሤ ዓለሙ ናቸው።
ስፖርትን በኅብረት መሥራት ብቁ አካላዊ ቁመና ከመገንባት ባለፈ ማኅበራዊ ትስስራቸውን እንዳጠናከረላቸውም አብራርተዋል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሠልጣኙ ደጀን ታዲዮስ
የትኛውም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲደረግ የባለሙያ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ባሉ 26 ሕዝባዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ማኅበረሰቡ ሰፖርታዊ እንቅስቃሴ እየሠራ እንደኾነ የከተማዋ ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ አስታውቋል።
የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ደረጃቸውን ጠብቀው አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል እድሳት እየተደረገላቸው መኾኑንም የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ማሩ ሙሐመድ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ተስፋዬ ጋሹ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here