ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአራተኛ ዙር የሻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታ ተጠባቂ ጨዋታዎች ተደርገዋል። በአንፊልድ ሊቨርፑልን የገጠመው ሪያል ማድሪድ ሽንፈት ገጥሞታል። ሊቨርፑል 1ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ ማክአሊስተር ግቧን አስቆጥሯል።
ሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ በፒኤስጂ እና ባየር ሙኒክ መካከል የተካሄደው ነው። ጨዋታው 2ለ1 ሲጠናቀቅ አሸናፊው ባየር ሙኒክ ሆኗል።
በሌሎቹ ጨዋታዎች ቶተንሃም ኮፐንሃገንን በ4ለ0 ሰፊ ግብ ልዩነት ረትቷል። አትሌቲኮ ማድሪድ ዩኔን ሴንት ግሊዮስን 3ለ1፣ ሞናኮ ቦዶ ግሊምትን 1ለ0 አሸንፈዋል።
ኦሎምፒያኮስ ከፒኤስቪ እና ስፖርቲንግ ከጁቬንቱስ ደግሞ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በዋሴ ባየ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



