ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አራተኛ ዙር ጨዋታ ዛሬ ሲካሄድ 18 ቡድኖች ዘጠኝ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ።
የጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየርሙኒክ ካለፈው ዓመት የቻምፒዮንስ ሊጉ አሸናፊ ፓሪሴንት ዥርሜን ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ጠንካራው ፓሪሴንት ዥርሜን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ዓመት የአውሮፓ ዋንጫን ለማሳካት ችሏል። ክለቡ ከፍተኛ ወጭ በማድረግ እና የተጨዋቾች ግዥ በመፈጸም ያደረገው ጥረት የቻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ በማንሳት አሳክቷል።
ክለቡ በኳታር ሃብታሞች ከተያዘ በኋላ ተወዳዳሪነቱ እንዲያድግ በተደረገው ጥረት ጥሩ ተፎካካሪ መኾን የቻለ እና ዋንጫውን ማሳካት የቻለ ክለብም ነው።
ፒኤስጅ በዚህ ዓመት ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሦስቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ በዘጠኝ ነጥብ ቀዳሚ ነው። አትላንታን 4ለ0፣ ባርሴሎናን 2ለ1 እና ባየር ሊቨርኩሰንን 7ለ2 ያሸነፈበት ጨዋታ ቡድኑ ያለበትን ብቃት አመላካች ናቸው።
የዛሬ ተጋጣሚው ባየርሙኒክ በሻምፒዮንስ ሊጉ ከስኬታማ ክለቦች መካከል አንዱ ነው። ውድድሩን ስድስት ጊዜ አሸናፊው ነው።
በዋንጫ ብዛትም ከሪያል ማድሪድ እና ኤሲ ሚላን በመቀጠል ከሊቨርፑል ጋር በሦስተኛ ደረጃ ታሪክ የሚጋራ ክለብም ነው።
ባየር ሙኒክ 11 ጊዜም የፍጻሜ ጨዋታዎችን ተጫውቷል። ይህም ከሪያል ማድሪድ በመቀጠል በሁለተኛነት ከኤሲ ሚላን ጋር የሚጋራውን ታሪክ መጻፍም ችሏል።
በዚህ ዓመት በቻምፒዮንስ ሊጉ ባካሄዳቸው ሦስት ጨዋታዎች ሁሉንም አሸንፎ በተመሳሳይ ዘጠኝ ነጥብ ይዟል። ክለቡ ቼልሲን 3ለ1፣ ፓፎስን 5ለ1 እና ክለብ ብሩጅን 4ለ0 ማሸነፍ የቻለ ጠንካራ አቋም ላይ ይገኛል።
ክለቦቹ በተጋጣሚዎቻቸው ላይ በርካታ ግቦችን የሚያስቆጥሩ በመሆናቸው ምሽት እርስ በእርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ለእግር ኳሱ ድምቀት እንደሚሆን ይጠበቃል። ጨዋታውም ምሽት 5፡00 ላይ መካሄድ ይጀምራል።
በምስጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
የምሽቱ የእግር ኳስ ድምቀት በፈረንሳይ!