ባሕር ዳር: ጥር 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ እየተወዳደረ የሚገኘው ዜድ ኤፍ ሲ የቅዱስ ጊዮርጊሱን የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈርም እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆቱ የሚታወስ ነው፡፡ አቤል ያለው ሊጠናቀቅ በተቃረበው የግብጽ የዝውውር ጊዜ ዜድ አፍ ሲን ተቀላቅሏል፡፡
በዚህም ከሳላሃዲን ሰዒድ ፣ ሽመልስ በቀለ ፣ ዑመድ ኡኩሪ እና ጋቶች ፓኖም በመቀጠል 5ኛው በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወት ኢትዮጵያዊ ተጫዋች መኾን ችሏል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!