ኤል ክላሲኮ በቤርናባው

0
7
ባሕር ዳር: ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ላሊጋ 10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተወዳጁ ኤል ክላሲኮ በቤርናባው ይካሄዳል፡፡ የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ኤል ክላሲኮ መርሐ ግብር መሪነትን ለማስጠበቅ እና መሪነትን ለመረከብ የሚደረግ ጨዋታ ይኾናል፡፡
ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና የሚያደርጉት የላሊጋ መርሐ ግብር በዓለማችን የእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
ላሊጋውን በ24 ነጥቦች የሚመሩት ሎስ ብላንኮቹ መሪነታቸውን ለማስጠበቅ ይጫዎታሉ፡፡
በአንጻሩ 22 ነጥቦችን ሰብስቦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባርሴሎና ጨዋታውን አሸንፎ መሪነቱን ከሪያል ማድሪድ ለመረከብ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በቅርብ ካደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች መካከል አምስቱንም ያሸነፈው ባርሴሎና ነውና የማሸነፍ ቅድመ ግምቱን ወስዷል፡፡
ማርካ በድረ ገጹ ከሁለት ቀናት በፊት እንዳስነበበው የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች የሳንቲያጎ ቤርናባው ስታዲየምን ሙሉ የሚያካልል ባነር ይይዛሉ፡፡ የባነሩ መልዕክትም “ታላቅነት” የሚል መልዕክት የያዘ ነው ተብሏል፡፡
ደጋፊዎቹ የስታዲየሙን ጣራ ዘግተው ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች እያሳዩ ነው፡፡
ጨዋታው ምሽት 12፡15 ላይ ሲጀምር ጨዋታውን ሴሳ ሶቶ ግራዶ በመሐል ዳኝነት ይመሩታል፡፡
በታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here