የሮናልዶ ነገር!

0
14
ባሕር ዳር: ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፖርቱጋላዊ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ማስደመሙን ቀጥሏል። ትናንት ምሽት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሀንጋሪን የገጠመችው ፖርቱጋል ነጥብ ተጋርታለች። ሁለት እኩል በተጠናቀቀው በዚህ ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የፖርቱጋልን ግቦች አስቆጥሯል።
ተጫዋቹ በቅርብ አራት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። 40ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው ኮከብ እግሮቹ ከመዛል ይልቅ አሁንም ግብ ማምረታቸውን ቀጥለዋል።
ሀንጋሪ ላይ ሁለት ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ብዙ ግብ ያስቆጠረ ቀዳሚው ተጫዋች ኾኗል። የጓቲማላው ካርሎስ ሩይዝ በ39 ግቦች ክብረወሰን ይዞ ነበር።
ሮናልዶ 39 ግብ ደርሶ ተጋርቶ ከቆየ በኋላ ትናንት ሁለት ግብ አስቆጥሮ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 41 ግብ በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን ተረክቧል።
ለፖርቱጋል ያስቆጠራቸው አጠቃላይ ግቦችም 143 ደርሰዋል። በእግር ኳስ ሕይወቴ ያስቆጠርኳቸው ግቦች 1000 መድረስ አለባቸው ያለው ይህ ተጫዋች አሁን የግቦቹ ብዛት 948 ደርሰዋል። ዕቅዱ ለመድረስ 52 ግቦች ይቀሩታል ማለት ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here