በአዲስ አበባ ከተማ የሕዳሴ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መቻል ለዋንጫ ደርሰዋል።

0
30
ባሕር ዳር: መስከረም 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ስድስት ክለቦችን ሲያፋልም የቆየው ‎የአዲስ አበባ ከተማ የሕዳሴ ዋንጫ ጨዋታ የፍጻሜ ተፋላሚዎችን ለይቷል።
በዚህ ውድድር ፋሲል ከነማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መቻል፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪከ ተሳትፈዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስን እና መቻልን ለዋንጫ ሽሚያ ያበቁት ሁለት ጨዋታዎችም ዛሬ ተካሂደዋል። በተጠባቂው የሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን 3ለ2 አሸንፏል።
በመቻል እና ኢትዮ ኤሌክትረክ መካከል የተካሄደው ጨዋታ ደግሞ በመቻል 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የሕዳሴ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የፊታችን እሑድ ይደረጋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here