ባሕር ዳር: መስከረም 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የደረጃ ለውጥ የሚያስከትሉ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
ቀን 10 ሰዓት ላይ አስቶንቪላ ከበርንሌይ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ዎልቭስ ከብራይተን እና ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ ይጫወታሉ።
በተለይ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ ቀን 10 ሰዓት እንዲኹም ማንቸስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ ምሽት 12፡30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ክሪስታል ፓላስ እስካኹን ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፎ፣ በሦስቱ አቻ በመውጣት እና 12ነጥብ በመያዝ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈም ነጥቡን 15 በማድረስ በሊቨርፑል በግብ ክፍያ ብቻ ተበልጦ ሦስተኛ ደረጃን ይይዛል።
በሌላ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ ወደ አምስተኛ ደረጃ ከፍ ሊያደርገው የሚያስችለውን ጨዋታ ምሽት
12፡30 በብሬንትፎርድ ሜዳ ያደርጋል።
ማንቸስተር ሲቲ እስካኹን ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች በሦስቱ አሸንፏል። በሁለቱ ተሸንፎ እና በአንዱ አቻ ተለያይቶ 10 ነጥብ ይዟል። የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ደረጃውን ወደ አምስት ከፍ ማድረግ ያስችለዋል።
ባለሜዳው ብሬንትፎርድ ደግሞ ከስድስት ጨዋታዎች በሁለቱ አሸንፎ፣ በሦስቱ ተሸንፎ እና በአንዱ አቻ ተለያይቶ በሰባት ነጥብ ደረጃው 14ኛ ነው።
ሊጉን አርሰናል በ16 ነጥብ ሲመራ ሊቨርፑል በ15፣ ቶትንሃም ደግሞ በ14 ቀጣዮችን ደረጃዎች ይዘዋል።
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!