ታላላቅ ክለቦች የሚገናኙበት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

0
53
ባሕር ዳር፡ መስከረም 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬም የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል አርሰናል ኦሎምፒያኮስን ወደ ሜዳው ይጋብዛል። ለ13ኛ ጊዜ የሚገናኙበትን ጨዋታም ነው።
ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት እኩል የመሸናነፍ ታሪክ ነው ያላቸው፤ እኩል ስድስት ጊዜ እርስ በእርስ ተሸናንፈዋል።
ዛሬ በሚደረገው ጨዋታ አርሰናል በሜዳው የተሻለ እንደሚኾን ቢጠበቅም ወደ እንግሊዝ ተጉዞ የማሸነፍ መልካም ታሪክ ያለው የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ ታሪኩን ሊደግም ይችላል በሚልም ይጠበቃል።
የአሠልጣኝ ሚኬል አርቴታን ቡድን የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ በ2019/20 ከውድድሩ እንዲሰናበት ያደረገው ሲኾን አርሰናል በፊናው በ2020/21 ኦሎምፒያኮስን ከውድድሩ ውጭ አድርጎታል።
ሌላው የስፔኑ ታላቅ ክለብ ባርሴሎና እና የፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ባርሴሎና እና ፓሪስ ሴን ዠርሜን በአውሮፓ ውድድሮች 16 ጊዜ ተገናኝተዋል። በዚህም የመሸናነፍ ታሪካቸው የተቀራረበ ነው። ባደረጓቸው 15 ጨዋታዎች ባርሴሎና ስድስት ጊዜ ሲያሸንፍ ፒ.ኤስ.ጂ አምስት ጊዜ አሸንፏል ቀሪው አቻ የተለያዩበት ነው።
ባርሴሎና በዚህ ዓመት የቻምፒየንስ ሊግ የውድድር ዘመን መክፈቻ ጨዋታ ላይ የተሻለ የመከላከል አቅም እንዳለው አሳይቷል።
ፒ.ኤስ.ጂ በቅርቡ በባርሴሎና ሜዳ በካምፕ ኑ ባደረጋቸው ጨዋታዎች የበላይነት እንዳለው ያሳያል። ቡድኑ በቅርቡ ሁለት ጊዜ ወደዚህ ሜዳ ተጉዞ ሁለቱንም 4 ለ1 በኾነ ውጤት አሸንፏል። ጉዳዩ ዛሬስ ይህን ይደግመዋል ወይ የሚለው ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ይታያል።
ፒ.ኤስ.ጂ በዚህ ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ በካምፕ ኑ ሜዳ በተከታታይ ሦሥት ጨዋታዎችን ያሸነፈ የመጀመሪያው ክለብ ይኾናል።
ምሽት ሌሎችም ተጠባቂ ጨዋታዎች ሲካሄዱ ምሽት 1፡45 ሰዓት ላይ ጋራባይ ከኮፐንሃገን ጋር ሲጫዎቱ ዩኒየን ሴንት-ጊሎይዝ ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር ይጫወታሉ።
ሌሎቹ ጨዋታዎች ደግሞ የሚደረጉት ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ሲኾን ባየር ሌቨርኩሰን ከፒ.ኤስ.ቪ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከአትሌቲክ ክለብ፣ ሞናኮ ከማንቸስተር ሲቲ፣ ናፖሊ ከስፖርቲንግ፣ ቪያሪያል ከዩቬንቱስ ጋር ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here