የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዛሬ መርሐ ግብሮች፦

0
32
ባሕር ዳር: መስከረም 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ምሽት ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ከጨዋታዎች መካከል ሊቨርፑል ወደ ቱርክ ተጉዞ ጋላታሳራይን የሚገጥምበት ጨዋታ አንዱ ነው።
ሊቨርፑል በዚህ የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ጨዋታ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር አድርጎ 3ለ2 አሸንፏል። ጋላታሳራይ ደግሞ በጀርመኑ ፍራንክፈርት 5ለ1 ተሸንፎ ነው ይህን ጨዋታ የሚያደርገው።
ሪያል ማድሪድ ወደ ካዛኪስታን አምሮቶ ከካይራት ጋር ይጫወታል። ማድሪዶች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከማርሴ ጋር አድርገው ማሸነፋቸው ይታወሳል። ነገር ግን በሳምንቱ መጨረሻ በማድሪድ ደርቢ በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፋቸው ይታወሳል።
በሌሎች ጨዋታዎች፦
👉 ፓፎስ ከባየር ሙኒክ
👉ቼልሲ ከቤኔፊካ
👉ኢንተር ሚላን ከስላቪያ ፕራግ
👉አትሌቲኮ ከፍራንክ ፈርት
👉አትላንታ ከክለብ ብሩጅ
👉ቦዶ/ ጊልሚት ከቶተንሃም
👉ማርሴይ ከአያክስ ሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here