ጆዜ በስታፎርድ ብሪጅ

0
18
ባሕርዳር፡ መስከረም 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ።
ምሽት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ጆዜ ሞሪንሆ ቤኔፊካን ይዘው ቼልሲን የሚገጥሙበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ጆዜ ሞሪንሆ በቼልሲ የሁለት የአሠልጣኝነት ጊዜያቸው ከቼልሲ ጋር የተለያዩ ዋንጫዎችን አንስተዋል።
ሌሎች ክለቦችን ይዘውም ቼልሲን የገጠሙባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ። በእነዚህ ጊዚያት ሰውየው በቼልሲ ደጋፊዎች ከደማቅ አቀባበል እስከተቃውሞ አስተናግደዋል።
ከጨዋታው በፊት ሃሳብ የሰጡት ሞሪንሆ “ቼልሲን ትልቅ አድርጌዋለሁ፣ እነሱም ትልቅ እንድኾን አግዘውኛል” ብለዋል።
ቼልሲ በልቤ ውስጥ ቢኾንም አሁን ግን ቼልሲን ማሸነፍ ነው የምፈልገው፤ የቼልሲ ደጋፊዎች በበጎ ከተቀበሏቸው በጎ ለመመለስ ዝግጁ እንደኾኑም ነው የተናገሩት።
ጨዋታው ምሽት 4:00 ሰዓት ይደረጋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here