ዌስትሃም ዩናይትድ አሠልጣኙን አሰናበተ።

0
23
ባሕር ዳር፡ መስከረም 17 /2018 ዓ.ም (አሚኮ)በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ አሠልጣኝ ግርሃም ፖተርን ከኃላፊነታቸው አንስቷል።
አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር በዌስትሃም ዩናይትድ ቤት የስምንት ወራት ቆይታ እንደነበራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
ዌስትሃም ዩናይትድ በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች በአራቱ ተሸንፏል። አንድ ጨዋታ ብቻ በማሸነፍ በደረጃ ሰንጠረዡ 19ኛ ላይ ይገኛል።
ዌስትሃም ዩናይትድ ባወጣው መግለጫ የዳይሬክተሮች ቦርድ ቡድኑ በፕሪምዬር ሊጉ ያለውን አቋም በፍጥነት ለማሻሻል እንዲረዳው ለውጥ አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል ብሏል። አሠልጣኙ ከመዶሻዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኗል። ለወደፊትም ስኬትማ እንዲኾኑ ተመኝቶላቸዋል። ክለቡ ተተኪያቸውን እየፈለገ መኾኑም ተመላክቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here