የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ “የሕዳሴ ዋንጫ” በሚል ይደረጋል።

0
11
ባሕር ዳር: መስከረም 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) “ሕዳሴ ዋንጫ” በሚል ስያሜ ከእሑድ ጀምሮ ይከናወናል።
የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው ይህ ውድድር ዘንድሮ በስምንት ክለቦች መካከል እንደሚከናወን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል። ፋሲል ከነማ በዚህ ውድድር እንደሚሳተፍ ታውቋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መቻል፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ ሌሎች የውድድሩ አካል ክለቦች ናቸው።
የምድብ ድልድሉም በእጣ ተለይቷል። ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፋሲል ከነማ ፣ አዳማ ከተማ እና መቻል በምድብ አንድ ተደልድለዋል።
ምድብ ሁለት ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮ. ኤሌክትሪክ፣ ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚጫወቱ የኤምኤን መረጃ ያሳያል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ “ሕዳሴ ዋንጫ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ውድድሩ የፊታችን እሑድ በአዲስ አበባ ስታዲየም መከናወን ይጀምራል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here