ሊዊስ ኤንሪኬ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝነት ሽልማትን አሸነፉ።

0
7
በዓለም የእግር ኳስ ሽልማት ከፍተኛው እንደኾነ የሚነገርለት የባላንዶር የሽልማት ሥነ ሥርዓት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እየተካሄደ ነው።
በ2025 የባላንዶር ሽልማት ሥነ ሥርዓት ምርጦቹ እየተሸለሙ ነው።
እስካሁን በተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት የፒኤስጂው አሠልጣኝ ሊዊስ ኤንሪኬ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለዋል። ኤንሪኬ በፈረንሳዩ ታላቅ ክለብ ታሪክ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን አሸንፈዋል።
በሴቶች ደግሞ የእንግሊዝ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሳሪና ዊግማን የአመቱ ምርጥ አሠልጣኝ ተሰኝተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here