ኢትዮጵያ እና ኬንያ የሚጠበቁበት የሴቶች 10ሺህ ሜትር

0
7
ባሕር ዳር፡ መስከረም 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በጃፓኗ ቶኪዮ ዛሬ ይጀመራል። በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን ከሚከናወኑ ውድድሮች መካከል የሴቶች 10ሺህ ሜትር ተጠባቂ ነው።
ውድድሩ የኢትዮጵያውያን የበላይነት የሚታይበት መኾኑን ታሪክ ይመሰክራል። በዓለም ሻምፒዮና ታሪክ በሴቶች 10ሺህ ሜትር ዘጠኝ የወርቅ ሜዳሊያዎችን በመሠብሠብ ውጤታማዋ ሀገር ናት።
በዛሬው ውድድር አትዮጵያ በአራት ሯጮች ትወከላለች። ያለፈው የዓለም ሻምፒዮና የርቀቱ አሸናፊ ጉዳፍ ጸጋየ በውድድሩ ቀጥታ ተሳታፊ በመኾኗ ነው ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ አራት ኾነው የሚሮጡት።
እጅጋየሁ ታየ፣ ጽጌ ገብረ ሰላማ እና ፎይተን ተስፋየ ከጉዳፍ በተጨማሪ ዛሬ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀዩን ሰንደቅ ከፍ ለማድረግ ጃፓን ተገኝተዋል።
ይህ “የኢትዮጵያውያን” የሚል ቅጽል የተሰጠውን ርቀት ኬንያውያን አትሌቶች ከኢትዮጵያ ለመንጠቅ ብርቱ ጥረት እንደሚያደርጉ ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትቷል።
በተለይ የኦሎምፒክ ባለድሏ ቺቤት ለኢትዮጵያውያኑ ፈታኝ ትሆናለች ተብሏል። የዩጋንዳ አትሌቶችም ጠንኳሮች በመኾናቸው የምሥራቅ አፍሪካን የእርስ በእርስ ፉክክር ከፍ እንደሚያደርጉት ተገምቷል።
ጉዳፍ ጸጋየ ውድድሩን በተከታታይ ለማሸነፍ፣ ኢትዮጵያም የበላይነቷን ለማስቀጠል የሚያደርጉት ውድድር ከቀኑ 9:30 ይጀምራል።
ዘጋቢ፦ አስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here