ኢትዮጵያ ከግብጽ

0
45
ባሕር ዳር: ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የእግር ኳስ ማጣሪያ ጨዋታ ያለባቸው ዋሊያዎቹ ዛሬ ወደ ፈርኦኖቹ መንደር ዘልቀዋል።
ምሽት 4፡00 ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ዋሊያዎቹ በምድብ አንድ ከተደለደሉት እና ምድቡን በበላይነት እየመሩ ከሚገኙት ፈርኦኖቹ ጋር ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ፈርኦኖች እንደ ፈረንጆቹ ዘመን መጋቢት 25/2025 ገጥመው 2ለ0 ተሸንፈዋል። ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ እስካሁን ስድስት ጊዜ ተጫውተዋል።
በእነዚህ ጨዋታዎችም ጅቡቲን 6ለ1 ከማሸነፍ ውጭ ሁለት ጊዜ ሽንፈት እና ሦሥት ጊዜ አቻ ወጥተዋል። ቡድኑ ኳስን ከመረብ ጋር የማገናኘት ችግር እንዳለበት ባለፉት ጊዜ ያደረጋቸው ጨዋታዎች ማሳያ ናቸው።
ከጊኒቢሳው እና ከሴራሊዎን ጋር ያለ ግብ መለያየቱ እና በቡርኪና ፋሶ 3ለ0 መሸነፉ ቡድኑ የግብ ክልል ደርሶ ኳስን ከመረብ የማገናኘት ችግር እንዳለበት በግልጽ ያሳያል።
አሠልጣኙ ታዲያ በዚህ ጨዋታ የተሻለ ጨራሽ አጥቂ ማሰለፍ እና የተከላካይ መስመራቸውን ማጠናከር ትልቅ ሥራ ነው።
ሴራሊዎንን 1ለ0፣ ኢትዮጵያን 2ለዐ፣ ቡርኪናፋሶን 2ለ1 በማሸነፍ ከጊኒቢሳው 1ለ1 አቻ በኾነ ውጤት የምድቡን ደረጃ እየመሩ የሚገኙት ግብጻዊያኑ ይህ ጨዋታ ካላቸው የሥነ ልቦና ጥንካሬ አንጻር ጨዋታውን የማሸነፍ ግምት ወስደዋል።
ጨዋታው በካይሮ ዓለም አቀፍ ስታድየም ይደረጋል።
ኢትዮጵያ በተደለደለችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የምድብ አንድ ውስጥ ግብጽ በ16 ነጥብ ስትመራ ቡርኪና ፋሶ በ11 ነጥብ ሁለተኛ፣ ሴራሊዮን በ8 ነጥብ ሦሥተኛ፣ ኢትዮጵያ በ6 ነጥብ አራተኛ፣ ጊኒቢሳው በግብ ከፍያ ተበልጣ በ6 ነጥብ አምስተኛ እና ጅቡቲ በ1 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ጨዋታ የምታገኘው ውጤት ወሳኝ በመኾኑ የተሻለ ውጤት ይዛ ለመውጣት ጥረት እንደምታደርግ ነው የሚጠበቀው።
በምሥጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here