ባሕርዳር: ጥር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚዎችን እየለየ ይገኛል።ዛሬም በሁለት ጨዋታዎች የሚቀጥል ሲኾን አዘጋጇ ኮትዲቯርን ከሴኔጋል የሚያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ሴኔጋል ያለፈው ዋንጫ ባለድል ስትኾን በዚህ የአፍሪካ ዋንጫም ሦስቱንም የምድብ ጨዋታዎች በማሸነፍ አስፈሪነቷን አሳይታለች።አዘጋጇ ኮትዲቯር በአንጻሩ በገዛ ድግሷ የበይ ተመልካች ለመኾን ጫፍ ደርሳ ነው የተመለሰችው።
በምድብ ጨዋታዎች ሦስት ነጥብ ብቻ በማስመዝገብ በቀጥታ ማለፍ አልቻለችም ነበር።በመጨረሻ በሌሎች ቡድኖች ውጤት ላይ ተመስርታ ጥሩ ሦስተኛ ኾና በውድድሩ ቆይታለች።
ጨዋታው ምሽት 5ሰዓት የሚጀመር ይኾናል።
በሌላ ጨዋታ ጠንካራዋ ኬፕ ቬርዴ ጥሩ ሦስተኛ ኾና ጥሎ ማለፉን ከተቀላቀለችው ሞርታንያ ይጋጠማሉ። ኬፕ ቬርዴ:- ግብጽ፣ጋናና ሞዛምቢክን በያዘው ጠንካራ ምድብ ፤የምድቡ የበላይ ኾና ነው ማጠናቀቅ የቻለችው።በዚህ ውድድር ከታዩ ጠንካራ ቡድኖች መካከል ተጠቃሽ ናት።
ሞዛምቢክ በበኩሏ በምድብ ጨዋታ ያሸነፈችው አንድን ብቻ ነው።በሁለቱ የተሸነፈች ሲኾን ጠንካራዋ አልጀሪያን በልጣ ጥሩ ሦስተኛ በመኾን ራሷን ጥሎ ማለፉ ውስጥ አግኝታለች።
ጨዋታው ምሽት 2 ሰዓት እንደሚጀምር ከቢቢሲ ስፖርት ዘገባ መረዳት ይቻላል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!