ባሕር ዳር: ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

ኮቢ ማይኑ በውሰት ዩናይትድን ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርቧል። ነገር ግን ዩናይትድ የተጫዋቹን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ጎል ጽፏል። አሠልጣኝ አሞሪም ማይኑን እንፈልገዋለን ብለዋል።

በቢቢሲ መረጃ መሠረት ዣቪ ሲሞንስ ወደ ቶትንሃም የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የሕክምና ምርመራውን አጠናቅቋል።

ሊቨርፑል ለኢሳክ ዝውውር 130ሚሊዮን ፓውንድ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ቴሌግራፍ አስነብቧል። የተጫዋቹ ዝውውር በቀጣዮቹ 48 ሰዓታት መልክ እንደሚይዝም ዘገባው ጨምሯል።

አሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከፌነርባቼ አሠልጣኝነት ተሰናብተዋል። ፌነርባቼ ለሻምፒዮንስ ሊግ ማለፍ አለመቻሉ በአሠልጣኙ ስንብት ምክንያት መኾኑን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

ቼልሲ ጋርናቾን ለማስፈረም ተስማምቷል። ተጫዋቹ በቀጣዮቹ ሰባት ዓመታት ለቼልሲ ለመጫወት ፊርማውን እንደሚያሰፍር ሜትሮ አስነብቧል።

ኒውካስትል ዩናይትድ ከጀርመኑ ስቱትጋርት አጥቂ ለማስፈረም ጫፍ ደርሷል። ኒክ ዋልቲሜድ የተሰኘው ይህ ተጫዋች በባየር ሙኒክ ሲፈለግ ነበር ብሏል ስካይ ስፖርት።

አርሰናል የፒሮ ሂንካፒን ዝውውር ለማጠናቀቅ ተቃርቧል። አርሰናል ተጫዋቹን በውስት ለማስፈረም እና በቀጣይ ተጫዋቹን በቋሚነት ከፈለገ 60 ሚሊዮን ዩሮ ለመክፈል ከሊቨርኩሰን ጋር ተስማምቷል።

ጎል አርሰናል እና ፖርቶ በኪዌር ዝውውር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስነብቧል። ተከላካዩ በአርቴታ ተመራጭ ባለመኾኑ ነው አርሰናልን የሚለቀው።

ሪያል ማድሪድ ኦፕሚካኖን በቅርበት እየተከታታለ ነው ሲል የዘገበው ደግሞ ስፖርት ቢልድ ነው። ተጫዋቹ የባየር ሙኒክ ውሉ በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቅ ይኾናል። ለተጨማሪ ጊዜ ለመቆየት እስካሁን ስምምነት ላይ አልደረሰም።

የቱርኩ ቢሽክታሽ ኦሊጎኖ ሾልሻየርን ከአሠልጣኝነት አንስቷል። ቢሽክታሽ በኮንፈረንስ ሊግ በቀድመ ጨዋታ በመሸነፉ ነው የቀድሞው የዩናይትድ ተጫዋች እና አሠልጣኝ ለስንብት የተዳረገው።