ባሕር ዳር: ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማምሻውን በዙሪክ በተካሄደው የመጨረሻ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በሴቶች 3ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ፋንታዬ በላይነህ አሸንፋለች። ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ አሸናፊውን ለመለየት አገባባቸው የተቀራረበ ስለነበር ዳኞች ረጅም ጊዜ ወስደው ከመረመሩ በኋላ አትሌት ፋንታዬ ማሸነፏን አረጋግጠዋል። አትሌት ፋንታዬ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 8:40.56 ፈጅቶባታል።
አትሌት ልቅና አምባው በ8:41.06 በመግባት አሜሪካዊቷን አትሌት ተከትላ ሦሥተኛ በመኾን አጠናቅቃለች ሲል የዘገበው አትሌቲክስ አፍሪካን ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን