አጫጭር የዝውውር ወሬዎች ከአሚኮ

0
79
ባሕር ዳር: ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
👉ማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር ወቅቱ ከመጠናቀቁ በፊት በአሠልጣኙ የማይፈለጉ ተጫዋቾችን ለመሸጥ ወስኗል። ተጫዋቾቹ ጋርናቾ፣ አንቶኒ፣ ሆይሉንድ እና ማለሲያ መኾናቸውን ታይምስ ስፖርት አሳውቋል።
👉በዘአትሌቲክ መረጃ መሠረት ቶትንሃም ሳቪኒዮን ከሲቲ ለማግኘት ተስፋ አድርጓል። ሲቲ ሮድሪጎን ከሪያል ማድሪድ ለማስፈረም ጥረት እያደረገ ነው። ዝውውሩ የሚሳካ ኮኾነም ሳቪኒዮ ከኢትሃድ እንደሚወጣ ይጠበቃል።
👉ጃንሉጅ ዱናሮማ ማንቸስተር ሲቲን የመቀላቀል ዕድሉ የሰፋ እንደኾነ እየተነገረ ነው። ፒኤስጂ ለጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ከ26 ሚሊዮን ፓውንድ ያነሰ የዝውውር ሂሳብ እንደሚፈልግ ያስነበበው ሚረር ፉትቦል ነው።
👉ኒውካስል ዩናይትድ የአጥቂ ፍለጋው መልስ አላገኘም። በክለቡ ለመቆየት የማይፈልገው የኢሳክን ጉዳይ መፍትሄም አልሰጠም። ክለቡ ከተለያዩ አጥቂዎች ጋር ስሙ እየተያያዘ ነው። የጁቬንቱሱ ዱሳን ቭላኾቪች ወደ ኒውካስል ሊዛወር ይችላል የሚሉ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ኒውካስል ቭላኾቪችን ማስፈረም እንደማይፈልግ መግለጹን ሰን ስፖርት ጽፏል።
👉የቼልሲው ኒኮላስ ጃክሰን ለባየር ሙኒክ ለመጫወት በግል መስማማቱን ሚረር ፉትቦል አስነብቧል። ሴኔጋላዊው አጥቂ በውሰት ነው የጀርመኑን ክለብ የሚቀላቀለው።
👉ኖቲንግሃም ፎረስት ብሬንዳን ሮጀርስን በአሠልጣኝነት ለመቅጠር ማቀዱን ዋን ፉትቦል የተሰኘ የመረጃ ምንጭ ዘግቧል። ኖቲንግሃም ኑኖ ስፕሪቶን ከአሠልጣኝነት እንደሚያነሳ በስፋት እየተወራ ነው።
👉ቶትንሃም፣ አስቶን ቪላ እና ኤሲሚላን የራብዮን ጉዳይ እየተከታተሉ ነው። ራብዮ ከክለብ ማርሴይ ጋር አለመግባባት ውስጥ እንደሚገኝ የጎል መረጃ ያሳያል።
👉 ቼልሲ ፊርሚን ሎፔዝን ለማስፈረም ለባርሴሎና ጥያቄ አቅርቧል። እንደ ሞንዶ ዲፖርቲቮ መረጃ ከኾነ ባርሴሎና ተጫዋቹ ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ የሚያቀረብ ከኾነ ከቼልሲ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነው።
👉ማርክ ጉሂን ለማዛወር የጸና አቋም ያለው ሊቨርፑል ከማንቸስተር ሲቲ ፉክክር እንደገጠመው የዘጋርዲያን መረጃ ዘገባ ያሳያል። ሲቲ አካንጅን ለመልቀቅ የሚፈልግ ሲኾን በምትኩ ጉሂን ቀዳሚ ምርጫው አድርጓል። የተጫዋቹ ምርጫ ግን ሊቨርፑል ነው ተብሏል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከርስቲያል ፓላስ የአካንጅን ፈላጊ ኾኗል።
ዘጋቢ:- አስማማው አማረ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here