ባሕር ዳር: ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ራስመስ ሆይሉንድ እንደ ናፖሊ እና አርቢ ሌፕዚግ ላሉ ክለቦች ለመጫዎት ከግዥ ይልቅ የውሰት ዝውውርን እንደሚመርጥ ግልጽ አድርጓል ሲል ፋብሪዚያኖ አገኘውት ያለውን መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል።
አርሰናል የአስቶን ቪላ አማካይ የኾነውን ሞርጋን ሮጀርስን ለማግኘት ጥያቄ እያቀረበ ነው። ይሁን እንጂ አስቶን ቪላ ይህንን እንግሊዛዊ ተጨዋች ለመሸጥ 80 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ እንደሚፈልግ ዘሰን አስነብቧል። እንደ ፍሎሪያን ፕሌቲንበርግ ዘገባ ዣቪ ሲሞንስ ወደ ቼልሲ ሊያመራ መኾኑን ተከትሎ አርቢ ሌፕዚግ ከ22 ዓመቱ የሊቨርፑል እንግሊዛዊ አማካይ ሃርቪ ኤሊዮት ጋር ተስማምቷል ተብሏል። ማርሴይ የ29 ዓመቱን የሊቨርፑል የግራ ተከላካይ ኮስታስ ጺሚካስን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው እና ተጨዋቹ በዚህ ክረምት ሊቨርፑልን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው ፉት መርካቶ ነው።
ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኖቲንግሃም ፎረስት የ23 ዓመቱን የስፔን የቀኝ ተከላካይ ሆሴ አንጀል ካርሞናን ከሴቪያ ለማስፈረም ድርድር ላይ ነው። ኖቲንግሃም ፎረስት የአስቶን ቪላን ተከላካይ ማቲ ካሽን እና ካርሞናን ወደ ክለቡ እንደገና ለመቀላቀል የሚያስችሉ መንገዶችን እየፈለገ እንደኾነ ዘአትሌቲክ አገኘውት ያለውን መረጃ ጠቅሶ አስነብቧል። ኤቨርተን የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት አንድ የክንፍ ተጨዋች ለማስፈረም ፍለጋ ላይ እንደኾነ የዘገበው ስካይ ስፖርት ከሳውዝሃምፕተን ታይለር ዲብሊንግን ለማስፈረም ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል ነው የተባለው።
የአስቶን ቪላው ስፔናዊ የግራ ተከላካይ አሌክስ ሞሬኖ የደሞዝ ቅናሽ ለማድረግ በመስማማቱ ወደ ጂሮና ሊዛወር መቃረቡን ዘአትሌቲክስ ጽፏል።
ሊቨርፑል ፍላጎቱን ያሳየበትን የብሬንትፎርዱን ናታን ኮሊንስን ቶተንሃም ለማስፈረም ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ኮት ኦፍሳይድ አስነብቧል።
ፉትቦል ኢንሳይደር እንደጻፈው ቦርንማውዝ የቼልሲውን ፈረንሳዊ የመሐል ተከላካይ አክሴል ዲሳሲን በውሰት ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ድርድር ጀምሯል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!