የኦሎምፒክ የሰላም ርግቦች

0
38
ባሕር ዳር: ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ወቅቱ ዓለም በጭንቅ ውስጥ የገባበት ዘመን ነበር፡፡
ዓለም በሁለት ተከፍሎ እርስ በእርስ ተገዳድሏል፡፡ አያሌ ኪሠራም ደርሶበታል። የአንደኛው የዓለም ጦርነት ዓለምን ሊቀይሩ የሚችሉ ብዙ ድንቅ ልጆችን ቀጥፏል፡፡ በዚህ ክስተት ታዲያ ንጹሐን ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ሁኔታው እጅግ አሰቃቂ ስለነበር ብዙዎች መልሶ እንዳይመጣ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡ ክስተቱ እየበረደ ቢሄድም የቃላት ጦርነቱ ስለነበር ይህን የሚያበርድ ሁኔታ ግን ግድ ይል ነበር፡፡ ያን አሰቃቂ ሁኔታ ምዕራፉን ለመዝጋት በየዘርፉ ከሚደረጉ የሰላም ውይይቶች በተጨማሪ በስፖርቱ ዘርፍም ሰላምን ዘላቂ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
በተለይም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተቋረጠውን የኦሎምፒክ ውድድር በማስጀመር ተራርቀው የነበሩ ሕዝቦችን ለማገናኘት እና ሰላምን ለመስበክ ጥረት ተደርጓል፡፡ በ1912 ዓ.ም ሰባተኛው የአንትወርፕ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከጦርነት ሥነልቦና መልስ የተካሄደ መድረክ ነው፡፡ ይህም ውድድር የተካሄደው ነሐሴ 8 ቀን ነበር። መድረኩ ታዲያ አዳዲስ ክስተቶችን ይዞ ብቅ አለ። ይህም የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት መድረክ ተደርጎ ታሪክ ያስታውሰዋል፡፡
በዚህ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ ብሎ የተውለበለበው የኦሎምፒክ ሰንደቅ ዓላማ ሰላምን ለዓለም የሰበከ ኾኖ ታይቷል፡፡ አምስት ቀለበት ያለው ይህ ሰንደቅ በጦርነት የፍርሀት ቆፈን ለነበሩ የሰላም ተምሳሌት ኾኖ ብቅ ብሏል፡፡
ከኦሎምፒክ ዶት ኮም የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ይህ የኦሎምፒክ ክስተት ዓለም እርስ በእርስ መወነጃጀል እና መነቃቀፉን ትቶ በአንድ ይዘምር ዘንድ የኦሎምፒክ መኃላ የተገባበት ነበር፡፡ ይህ የኦሎምፒክ ጨዋታ ያሳየን ሰላምን የሚሰብኩ ነጫጭ እርግቦችን ነው፡፡ እርግቦቹ በኦሎምፒክ መድረክ የሰላም ተምሳሌት ኾነው ለስፖርቱ ዘርፍ ማድመቂያ ሲኾኑ ዓለም ሰላም ትኾን ዘንድ ብዙዎች በሰማይ ላይ ከአንዣበቡ እርግቦች ጋር ተስፋ አድርገዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here