ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ ቤንጃሚን ሴስኮን ከአር ቢ ሌይፕዚሽ ማስፈረሙ ተገልጿል።በበርካታ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው ወጣቱ ኮኮብ የማንቸስተር ዩናይትድን ጥያቄ መቀበሉ ይታወሳል። ከጀርመን ወደ እንግሊዝ አቅንቶ የሕክምና ምርመራውን ያደረገውን ቤንጃሚን ሴስኮ የሕክምና ምርመራውን በማጠናቀቅ ስምምነቱን ፈርሟል።ጣልያናዊው ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንዳስነበበው ሴስኮ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት እስከ 2030 ድረስ የሚያቆየውን ውል ነው የፈረመው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን