ባሕር ዳር: ነሐሴ 3/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የነበረውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያጠናቀቀው ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ በኦልድ ትራፎርድ የጣልያኑን ፊዮሬንቲና ያስተናግዳል፡፡ ቀን 8:45 ሰዓት ላይ በሚደረገው ጨዋታ የቀድሞው የማንችስተር ዩናትድ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ ዳግም ወደ ኦልድ ትራፎርድ ይመለሳል፡፡በ12 ዓመታት የዩናትድ ቆይታው 545 ጨዋታችን ያደረገው ዴቪድ ደሂያ በኦልድ ትራፎረድ ደማቅ አቀባበል ይጠብቀዋል፡፡
የ34 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በ2012 ወደ ዩናይትድ ካመጡት አሰልጣኝ ሰር አሌከስ ፈረጉሰን ጋርም ተገናኝቷል፡፡በሌላ ጨዋታ ደግሞ በኢምሬትስ ዋንጫ አርሰናል ከአትሌቲክ ቢልባኦ ይገናኛል፡፡ባለፉት ሁለት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ሽንፈት ያጋጠመው አርሰናል ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እንደሚጫዎት ይጠበቃል፡፡ ጨዋታው ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ይጀምራል። አርሰናል ሊጉ ከመጀመሩ በፊት የሚያደርገው የመጨረሻ የአቋም መለኪያ ጨዋታውም ይኾናል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!