አጫጭር ስፖርታዊ ዘገባዎች -ከአሚኮ

0
63
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዋትፎርድ የተከላካይ መስመር ተጨዋቹን ማክስ አሌየን ከማንችስተር ሲቲ በውሰት ማስፈረሙን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
👉አስቶን ቪላ ኢቫን ጉሳንድን በ30 ሚሊዮን ፓውንድ
ከኒስን ማስፈረሙ ተዘግቧል።
👉 አርሰናል እና ኒውካስትል ዩናይትድን ጨምሮ የበርካታ ክለቦች የዝውውር ዒላማ የነበረው ቤንጃሚን ሴስኮ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ለመዘዋወር የሚያደርገውን ሂደት ለማፋጠን ደመወዙን ለመቀነስ መስማማቱ ስካይ ስፖርት ዘግቧል። ሴስኩ የሕክምና ምርመራውን ለማድረግ ማንቸስተር ገብቷል።
👉 ፋብሪዚያኖ እንዳስነበበው ማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂውን ራስመስ ሆይሉንድን በውሰት ለመልቀቅ ዝግጁ ኾኗል። ቤንጃሚን ሴስኮ ወደ ዩናይትድ የሚያደርገው ዝውውር ለመጨረስ በመቃረቡ ምክንያት ዴንማርካዊው አጥቂ ሆይሉንድ በቡድኑ ውስጥ ያለው ቦታ አጠያያቂ ነው።
👉 ማንቸስተር ዩናይትድ ከአሰልጣኝ ሮበን አሞሪም ጋር አለመግባባት ውስጥ የገባውን አሌሃንድሮ ጋራናቾን ለገበያ አቅርቧል። ቼልሲን ጨምሮ በርካታ ክለቦች የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው። ዘቴሌግራፍ እና ሌሎች ሚዲያዎች እንደዘገቡት ጋራናቾ ፍላጎቱ ቸልሲን መቀላቀል ነው።
👉 ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኮሞ ስፔናዊውን አጥቂ አልቫሮ ሞራታን ለማስፈረም ተስማምቷል።
👉 እንደ ሜል ዘገባ ወጣቱ አጥቂ ጎንዛሎ ጋርሺያ በሪያል ማድሪድ እስከ 2030 የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈራረም ተስማምቷል። አዲሱ ስምምነት የ1 ቢሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ የተካተተበት ነው። ይህም ክለቡ በተጫዋቹ ላይ ያለውን ትልቅ እምነት ያሳያል ተብሏል።
👉 የባርሴሎናው ተከላካይ ኢንጎ ማርቲኔዝ ወደ ሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ለመዛወር ስምምነት ላይ መድረሱ ተዘግቧል።
👉 የቼልሲው አጥቂ ክሪስቶፈር ንኩንኩ ከክለቡ ለመልቀቅ እየተዘጋጀ ነው። ንኩንኩ ከቼልሲ ጋር በድጋሚ የመጫወት እድል እንደሌለው ተገልጿል፡፡ ክለቡን የሚለቅበትን ጊዜ እየጠበቀ እንደኾነም ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here